የቢዝነስ ዓለም እጅግ ፈጣን በሆነ የለውጥ ጎዳና ላይ ይገኛል። በዚህ ወቅት የንግድ ተቋማት ዋጋ (Business Valuation) የሚተመነው የትናንትናውን ትርፍ ብቻ በመመልከት ሳይሆን የነገውን የመቀጠል አቅም እና የቴክኖሎጂ ዝግጁነትን መለኪያ በማድረግ ነው። የ “Business Valuation-ET” ዓምድ በዚህ እትሙ፣ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ካለው ግመታ ጋር ተያይዞ የንግድ መሪዎች ሊገነዘቧቸው የሚገቡ አዳዲስ የግምገማ ቀመሮችን በዝርዝር ያቀርባል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ዝግጁነት እሴት
በአሁኑ ወቅት የአንድ ኩባንያ ዋጋ የሚወሰነው ባለው ቋሚ ንብረት ብቻ ሳይሆን በዲጂታል ዳታ አያያዙ እና በ AI አጠቃቀሙ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI-driven models) በገበያ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ በመተንበይ እና የገንዘብ ፍሰት ጥራትን በማረጋገጥ በኩል ትልቅ እሴት ይጨምራሉ። አንድ ተቋም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ተግባራዊ ካደረገ፣ ለባለሀብቶች የሚኖረው ሳቢነት እና የሚሰጠው የዋጋ ተመን (Valuation Premium) ከባህላዊ ኩባንያዎች እጅግ የላቀ ይሆናል።
ESG እና የ IFRS ተፅእኖ
አዲሱ የ IFRS ዘላቂነትን ይፋ የማድረግ መስፈርት (Sustainability Disclosure Standards) ኩባንያዎች ስለ አካባቢ ጥበቃ፣ ማህበራዊ ኃላፊነት እና መልካም አስተዳደር (ESG) ሪፖርት እንዲያቀርቡ ያስገድዳል። ይህ ጉዳይ አሁን ላይ ከበጎ አድራጎትነት ባለፈ ቀጥተኛ የፋይናንስ ተፅእኖ አለው። ባለሀብቶች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋምና ግልፅ አሰራር ያለው ኩባንያ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ስለሚመርጡ፣ እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋማት በገበያው ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ያገኛሉ።
የስትራቴጂክ ፕሪሚየም ስሌት
ምንም እንኳን የዲሲኤፍ (Discounted Cash Flow) ስሌት መሰረታዊ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅታዊ የገበያ መዋቅር ውስጥ ግን በቂ አይደለም። አሁን ላይ “Strategic Premium” ወይም ኩባንያው ወደፊት ሊኖረው የሚችለው የገበያ ድርሻ እና የመስፋፋት አቅም (Scalability) ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። የተለያዩ ሃገራዊ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች በኢትዮጵያ ተግባራዊ መሆናቸውን ተከትሎ፣ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የራሳቸውን ዋጋ በአለምአቀፍ ስታንዳርድ መገምገም እና ለስትራቴጂክ እድገታቸው ተገቢውን ዋጋ ማግኘት ይኖርባቸዋል።



Leave a Reply